ጎንደር ቅ/ጽ/ቤት

አቶ ደምለዉ ነብዩ
የቅርንጫፍ ዳይሬክተር
- የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ መገኛ/አድራሻ :- ጎንደር ከተማ አስተዳደር ማራኪ ክፍለ ከተማ
- ስ.ቁ ፦ +25158116626
- ኢሜል፡- gonderbranch23@gmail.com
-
የቅርንጫፍ ዳይሬክተር :- አቶ ደምለው ነብዩ
ስልክ - 0918785001 -
ኢሜል፡ ademelew@yahoo.com
የጎንደር ቅ/ጽ/ቤት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእፅዋት ዘር እና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር
ኳራንታይን ባለስልጣንን ለማቋቋም ያወጣውን አዋጅ 208/2006 እና የእፅዋት ዘር አዋጅ 782/2005 ተከትሎ
በ2007 ዓ/ም 20 የቴክኒክና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞችን በመያዝ በቅ/ጽ/ ቤትነት ተቋቋመ፡፡ ቅ/ጽ/ቤቱ ከ1995 እስከ 1996
ዓ/ም ድረስ ‹‹ጎንደር የእፅዋት ዘር ላብራቶሪ›› በሚል ስያሜ ተጠሪነቱን ለፌዴራል የግብርና ግብዓት ተቋም አድርጎ
በአንድ ኃላፊና አንድ የቴክኒክ ባለሙያ ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በኋላም በክልሉ ግብርና ቢሮ ስር በመሆን
እስከ 2006 ዓ/ም ድረስ የግብርና ግብዓቶችን በተለይም የዘር ጥራት ቁጥጥር ስራ ሲያከናውን ቆይቷል::
የጎንደር ቅ/ጽ/ቤት ለጎንደር ከተማ፣ ደብረ ታቦር ከተማ፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ
ጎንደር ዞኖች ስር ለሚገኙ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች አገልግሎት ይሰጣል፡፡
የጎንደር ቅ/ጽ/ቤት መቀመጫው በአማራ ብሄራዊ ክላዊ መንግስት በማዕከላዊ ጎንደር ዋና ከተማ በሆነችው
ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ነው፡፡ ጎንደር ከተማ ከክልሉ ርዕሰ መዲና ባህር ዳር 180 ኪ/ሜ እንዲሁም ከአዲስ አበባ 750
ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ በስራ ክልሉ ውስጥ ዘርን በማባዛት፣በማምረት ፣በማዘጋጀትና በግብይት፤ በፀረ ተባይ ኬሚካልና የአፈር
ማዳበሪያ ንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ የግልም ሆነ የመንግስት ዘር አምራቾችና ለሌሎች የግብርና ግብዓት አቅራቢዎች
ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ያድሳል፣ህጋዊ አሰራሮችን ያልተከተሉ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ ይሰርዛል፤
ሁለንተና የግብርና ግብዓት ጥራት ማረጋገጥ ስርዓት እንዲተገበርና ጥራት ቁጥጥር ስርዓትን ለማሻሻል የሚረዱ
የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ይቀርፃል፤ በግብርና ግብዓት ማምረትና ግብይት ስራ ላይ የተሰማሩ በሀገሪቱ ህግ መሰረት
መስራታቸውን ይከታተላል ያረጋገጣል፤ በስራ ክልሉ ውስጥ በዘር ማምረት፣ በማባዛት ወይም በግብይት እና በፀረ
ተባይ ኬሚካልና የአፈር ማዳበሪያ ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ማንኛውም ሰው አስተማማኝ የጥራት ቁጥጥር
እየተካሄደበት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ለጥራት ቁጥጥር የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስራዎች መካሄዳቸውን
ይከታተላል፡፡ በክልሉ ውስጥ በሚመረቱ ዘሮች እና የፀረ ተባይ ኬሚካልና የአፈር ማዳበሪያ ላይ ጥራትን ለማረጋገጥ
በመስክና በክምችት ናሙና ተወስዶ እንዲመረመር ያደርጋል፣ በጥራት ደረጃ መስፈርት መሰረት የጥራት ደረጃውን
ያሟላውንና ያላሟላውን ይለያል፣ የሁሉንም ዘር ደረጃዎች መለያ ምልክት (ታግ) ለይቶ ለተጠቃሚዎች እስኪደርስ
ድረስ ሂደቱን በባለቤትነት ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፡፡ ለፀረ ተባይ ኬሚካል፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ ዘር አምራቾች፣
አዘጋጆች አቅራቢዎች፣ ሻጮችና ተጠቀሚዎች፤ በጥራት ደረጃዎች አጠባበቅና በአዋጆች በማስፈፀሚያ ደንቦችና
መመሪያዎች አተገባበር ረገድ ስልጠናዎች እንዲሰጡ፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች እንዲነደፉ ያደርጋል፡፡
የጥራት መጓደልን አስመልክቶ ከተጠቃሚዎች ለሚነሱ ማናቸውም ቅሬታዎች የተጠኑ ምላሾችን ይሰጣል፡፡
ምርታማነታቸውና ውጤታማነታቸው የወረደ ዘሮች፣ ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችና ማዳበሪያዎች ከስርጭት እንዲወጡ
ያደርጋል፡፡ በመስክና በክምችት የጥራት ቁጥጥር ተካሂዶባቸው የጥራት ደረጃ መስፈርቶችን ያላሟላ ዘር፣ ፀረ-ተባይ
ኬሚካሎችና ማዳበሪያዎች አጠቃቀምና አወጋገድ ይከታተላል፣ የዘርና ሌሎች ግብዓቶችን ጥራት ቁጥጥርና
የማረጋገጥ ጉዳዮችን አስመልክቶ የስራ ክልሉን ይወክላል፤ በስራ ክልሉ ውስጥ የሚካሄድ ህገ ወጥ የዘር፣ ፀረ ተባይና
ማዳበሪያ ንግድና ዝውውርን ይከታተላል፤ ህገ-ወጦችን ከሚመለከታቸው የህግ አካላት ጋር በመሆን ለህግ
እንዲቀርቡ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
በመሆኑም ቅ/ጽ/ቤቱ በአሁኑ ሰዓት የመስክ ሰብል፣ የአትክትና ፍራፍሬ፣ የደንና መኖ ዘር፣ የፀረ ተባይና ማዳበሪያ
ጥራትን በመስክና በላብራቶሪ የመቆጣጠር ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በእፅዋት ዘር ማባዛት፣ ማምረት፣
ማዘጋጀት እና በግብይት፣ ፀረ ተባይና ማዳበሪያንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ የግልም ሆነ የመንግስት ዘር አምራቾችና
አቅራቢዎች ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የመስጠት፣ የማደስ፣ እንዲሁም ህጋዊ አሰራሮችን ያልተከተሉ ሆነው
በሚገኙበት ጊዜ የመሰረዝ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡
