ደሴ ቅ/ጽ/ቤት

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ መገኛ/አድራሻ

ደሴ ከተማ አስተዳደር ደቡብ ወሎ ዞን አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ;- ቧንቧ ክፍለ ከተማ…. -ሞባይል፡ -የቢሮ፡ +251333111035 ፖስታ ፡ ኢሜል፡ dessieplantseedlab@gmail.com የቅርንጫፍ ዳይሬክተር ስም - ብርሃኔ ገብሬ ኃብተማርያም ስልክ - 0914066057 ኢሜል

ደሴ ቅ/ጽ/ቤት
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የእፅዋት ዘር አዋጅ 782/2005 እና የእፅዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር
ኳራንታይን ባለስልጣን መቋቋሚያ አዋጅ 208/2006 መውጣትን ተከትሎ በ2007 ዓ/ም በአዲስ መልኩ የሰው
ሃይልና የተለያዩ አዳዲስ የስራ ዘርፎችን አካቶ ተቋቋሟል፡፡ ከ2007 በፊት የደሴ እፅዋት ዘር ላብራቶሪ በሚል ስያሜ
ተጠሪነቱ ለፌዴራል የግብርና ግብዓት ተቋም ሆኖ የዘር ጥራት ማረጋገጥ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
የደሴ ቅ/ጽ/ቤት በደቡብሎ ዞን መቀመጫ ደሴ ከተማ የሚገኝ ሲሆን በዙሪያው ለሚገኙ ለደሴ ከተማ አስተዳደር፣
ወልድያ ከተማና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ለደቡብ ወሎ፣ሰሜን ወሎ፣ ዋግ ኸምራና ኦሮሞ ብሄረሰብ
አስተዳደር ዞኖች ስር ለሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች አገልጎሎት ይሰጣል፡፡ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ከባህርዳር
546 ኪ/ሜ እና ከአዲስ አበባ 400 ኬ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ በስራ ክልሉ ውስጥ ዘርን በማባዛት፣በማምረት ፣በማዘጋጀትና በግብይት፤ በፀረ ተባይ ኬሚካልና የአፈር
ማዳበሪያ ንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ የግልም ሆነ የመንግስት ዘር አምራቾችና ለሌሎች የግብርና ግብዓት አቅራቢዎች
ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ያድሳል፣ህጋዊ አሰራሮችን ያልተከተሉ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ ይሰርዛል፤
ሁለንተና የግብርና ግብዓት ጥራት ማረጋገጥ ስርዓት እንዲተገበርና ጥራት ቁጥጥር ስርዓትን ለማሻሻል የሚረዱ
የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ይቀርፃል፤ በግብርና ግብዓት ማምረትና ግብይት ስራ ላይ የተሰማሩ በሀገሪቱ ህግ መሰረት
መስራታቸውን ይከታተላል ያረጋገጣል፤ በስራ ክልሉ ውስጥ በዘር ማምረት፣ በማባዛት ወይም በግብይት እና በፀረ
ተባይ ኬሚካልና የአፈር ማዳበሪያ ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ማንኛውም ሰው አስተማማኝ የጥራት ቁጥጥር
እየተካሄደበት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ለጥራት ቁጥጥር የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስራዎች መካሄዳቸውን
ይከታተላል፡፡ በክልሉ ውስጥ በሚመረቱ ዘሮች እና የፀረ ተባይ ኬሚካልና የአፈር ማዳበሪያ ላይ ጥራትን ለማረጋገጥ
በመስክና በክምችት ናሙና ተወስዶ እንዲመረመር ያደርጋል፣ በጥራት ደረጃ መስፈርት መሰረት የጥራት ደረጃውን
ያሟላውንና ያላሟላውን ይለያል፣ የሁሉንም ዘር ደረጃዎች መለያ ምልክት (ታግ) ለይቶ ለተጠቃሚዎች እስኪደርስ
ድረስ ሂደቱን በባለቤትነት ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፡፡ ለፀረ ተባይ ኬሚካል፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ ዘር አምራቾች፣
አዘጋጆች አቅራቢዎች፣ ሻጮችና ተጠቀሚዎች፤ በጥራት ደረጃዎች አጠባበቅና በአዋጆች በማስፈፀሚያ ደንቦችና
መመሪያዎች አተገባበር ረገድ ስልጠናዎች እንዲሰጡ፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች እንዲነደፉ ያደርጋል፡፡
የጥራት መጓደልን አስመልክቶ ከተጠቃሚዎች ለሚነሱ ማናቸውም ቅሬታዎች የተጠኑ ምላሾችን ይሰጣል፡፡
ምርታማነታቸውና ውጤታማነታቸው የወረደ ዘሮች፣ ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችና ማዳበሪያዎች ከስርጭት እንዲወጡ
ያደርጋል፡፡ በመስክና በክምችት የጥራት ቁጥጥር ተካሂዶባቸው የጥራት ደረጃ መስፈርቶችን ያላሟላ ዘር፣ ፀረ-ተባይ
ኬሚካሎችና ማዳበሪያዎች አጠቃቀምና አወጋገድ ይከታተላል፣ የዘርና ሌሎች ግብዓቶችን ጥራት ቁጥጥርና
የማረጋገጥ ጉዳዮችን አስመልክቶ የስራ ክልሉን ይወክላል፤ በስራ ክልሉ ውስጥ የሚካሄድ ህገ ወጥ የዘር፣ ፀረ ተባይና
ማዳበሪያ ንግድና ዝውውርን ይከታተላል፤ ህገ-ወጦችን ከሚመለከታቸው የህግ አካላት ጋር በመሆን ለህግ
እንዲቀርቡ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
በመሆኑም ቅ/ጽ/ቤቱ በአሁኑ ሰዓት የመስክ ሰብል፣ የአትክትና ፍራፍሬ፣ የደንና መኖ ዘር፣ የፀረ ተባይና ማዳበሪያ
ጥራትን በመስክና በላብራቶሪ የመቆጣጠር ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በእፅዋት ዘር ማባዛት፣ ማምረት፣
ማዘጋጀት እና በግብይት፣ ፀረ ተባይና ማዳበሪያንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ የግልም ሆነ የመንግስት ዘር አምራቾችና
አቅራቢዎች ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የመስጠት፣ የማደስ፣ እንዲሁም ህጋዊ አሰራሮችን ያልተከተሉ
ሆነው በሚገኙበት ጊዜ የመሰረዝ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

Scroll to Top