ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት
የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ መገኛ/አድራሻ :- ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሰሜን ጎጃም ዞን አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት - ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ - ስልክ -ሞባይል፡ -የቢሮ፡ +251******* ፖስታ ኢሜል፡ የቅርንጫፍ ዳይሬክተር ስም - አየነው ንጋቱ - ስልክ - 0986915648 - ኢሜል፡ Ayenew153@gmail.com
ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት
የባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእፅዋት ዘር እና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች
ጥራት ቁጥጥር ኳራንታይን ባለስልጣንን ለማቋቋም ያወጣውን አዋጅ 208/2006 ተከትሎ በ2007 ዓ/ም
20 የቴክኒክና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞችን በመያዝ በቅ/ጽ/ ቤትነት ተቋቋመ፡፡ ቅ/ጽ/ቤቱ ከ1995 እስከ 2006
ዓ/ም ድረስ ‹‹የእፅዋት ዘር ላብራቶሪ›› በሚል ስያሜ በቀድሞው የምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ
ዱርቤቴ ከተማ ተጠሪነቱን ለፌዴራል የግብርና ግብዓት ተቋም እና ቀጥሎም ለክልሉ ግብርና ቢሮ አድርጎ
ከአንድ ኃላፊና አንድ የቴክኒክ ባለሙያ ጀምሮ የሙያተኛ ቁጥርን ወደ አራት በማሳደግ አገልግሎት ሲሰጥ
ቆይቷል::
ቅ/ጽ/ቤቱ በስራ ክልሉ ውስጥ ዘርን በማባዛት፣በማምረት ፣በማዘጋጀትና በግብይት፤ በፀረ ተባይ ኬሚካልና
የአፈር ማዳበሪያ ንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ የግልም ሆነ የመንግስት ዘር አምራቾችና ለሌሎች የግብርና
ግብዓት አቅራቢዎች ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ያድሳል፣ህጋዊ አሰራሮችን ያልተከተሉ
ሆነው በሚገኙበት ጊዜ ይሰርዛል፤ ሁለንተና የግብርና ግብዓት ጥራት ማረጋገጥ ስርዓት እንዲተገበርና
ጥራት ቁጥጥር ስርዓትን ለማሻሻል የሚረዱ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ይቀርፃል፤ በግብርና ግብዓት ማምረትና
ግብይት ስራ ላይ የተሰማሩ በሀገሪቱ ህግ መሰረት መስራታቸውን ይከታተላል ያረጋገጣል፤ በስራ ክልሉ
ውስጥ በዘር ማምረት፣ በማባዛት ወይም በግብይት እና በፀረ ተባይ ኬሚካልና የአፈር ማዳበሪያ ንግድ ስራ
ላይ የተሰማራ ማንኛውም ሰው አስተማማኝ የጥራት ቁጥጥር እየተካሄደበት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
ለጥራት ቁጥጥር የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስራዎች መካሄዳቸውን ይከታተላል፡፡ በክልሉ ውስጥ
በሚመረቱ ዘሮች እና የፀረ ተባይ ኬሚካልና የአፈር ማዳበሪያ ላይ ጥራትን ለማረጋገጥ በመስክና
በክምችት ናሙና ተወስዶ እንዲመረመር ያደርጋል፣ በጥራት ደረጃ መስፈርት መሰረት የጥራት ደረጃውን
ያሟላውንና ያላሟላውን ይለያል፣ የሁሉንም ዘር ደረጃዎች መለያ ምልክት (ታግ) ለይቶ ለተጠቃሚዎች
እስኪደርስ ድረስ ሂደቱን በባለቤትነት ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፡፡ ለፀረ ተባይ ኬሚካል፣ የአፈር
ማዳበሪያ፣ ዘር አምራቾች፣ አዘጋጆች አቅራቢዎች፣ ሻጮችና ተጠቀሚዎች፤ በጥራት ደረጃዎች አጠባበቅና
በአዋጆች በማስፈፀሚያ ደንቦችና መመሪያዎች አተገባበር ረገድ ስልጠናዎች እንዲሰጡ፤ የግንዛቤ
ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች እንዲነደፉ ያደርጋል፡፡ የጥራት መጓደልን አስመልክቶ ከተጠቃሚዎች ለሚነሱ
ማናቸውም ቅሬታዎች የተጠኑ ምላሾችን ይሰጣል፡፡ ምርታማነታቸውና ውጤታማነታቸው የወረደ ዘሮች፣
ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችና ማዳበሪያዎች ከስርጭት እንዲወጡ ያደርጋል፡፡ በመስክና በክምችት የጥራት
ቁጥጥር ተካሂዶባቸው የጥራት ደረጃ መስፈርቶችን ያላሟላ ዘር፣ ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችና ማዳበሪያዎች
አጠቃቀምና አወጋገድ ይከታተላል፣ የዘርና ሌሎች ግብዓቶችን ጥራት ቁጥጥርና የማረጋገጥ ጉዳዮችን
አስመልክቶ የስራ ክልሉን ይወክላል፤ በስራ ክልሉ ውስጥ የሚካሄድ ህገ ወጥ የዘር፣ ፀረ ተባይና ማዳበሪያ
ንግድና ዝውውርን ይከታተላል፤ ህገ-ወጦችን ከሚመለከታቸው የህግ አካላት ጋር በመሆን ለህግ
እንዲቀርቡ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
በመሆኑም ቅ/ጽ/ቤቱ በአሁኑ ሰዓት የመስክ ሰብል፣ የአትክትና ፍራፍሬ፣ የደንና መኖ ዘር፣ የፀረ ተባይና
ማዳበሪያ ጥራትን በመስክና በላብራቶሪ የመቆጣጠር ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በእፅዋት ዘር
ማባዛት፣ ማምረት፣ ማዘጋጀት እና በግብይት፣ ፀረ ተባይና ማዳበሪያንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ የግልም ሆነ
የመንግስት ዘር አምራቾችና አቅራቢዎች ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የመስጠት፣ የማደስ፣
እንዲሁም ህጋዊ አሰራሮችን ያልተከተሉ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ የመሰረዝ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡:
