ደብረ ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ መገኛ/አድራሻ

ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሰሜን ሽዋ ዞን አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጣይቱ ክፍለ ከተማ…. ስልክ -ሞባይል፡ -የቢሮ፡ +251116376064 ፖስታ ኢሜል፡ dbseedqualityteam@gmail.com የቅርንጫፍ ዳይሬክተር ስም - አውግቸው ተሾመ ስልክ - 0911777063 ኢሜል፡ awgchew22@gmail.com

የደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በ2012 ዓ/ም የተቋቋመና ከሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች ያነሰ እድሜ ያለው ሲሆን
አገልግሎቱን ለደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደርና በሰሜን ሽዋ ዞን ስር ለሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች
ይሰጣል፡፡
ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በሰሜን ሽዋ ዞን መቀመጫ ደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኝ ሲሆን ከባህር ዳር በ685 ከ/ሜትርና
ከአዲስ አበባ በ130 ኬ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ በስራ ክልሉ ውስጥ ዘርን በማባዛት፣በማምረት ፣በማዘጋጀትና በግብይት፤ በፀረ ተባይ ኬሚካልና የአፈር
ማዳበሪያ ንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ የግልም ሆነ የመንግስት ዘር አምራቾችና ለሌሎች የግብርና ግብዓት አቅራቢዎች
ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ያድሳል፣ህጋዊ አሰራሮችን ያልተከተሉ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ
ይሰርዛል፤ ሁለንተና የግብርና ግብዓት ጥራት ማረጋገጥ ስርዓት እንዲተገበርና ጥራት ቁጥጥር ስርዓትን ለማሻሻል
የሚረዱ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ይቀርፃል፤ በግብርና ግብዓት ማምረትና ግብይት ስራ ላይ የተሰማሩ በሀገሪቱ ህግ
መሰረት መስራታቸውን ይከታተላል ያረጋገጣል፤ በስራ ክልሉ ውስጥ በዘር ማምረት፣ በማባዛት ወይም በግብይት
እና በፀረ ተባይ ኬሚካልና የአፈር ማዳበሪያ ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ማንኛውም ሰው አስተማማኝ የጥራት
ቁጥጥር እየተካሄደበት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ለጥራት ቁጥጥር የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስራዎች መካሄዳቸውን
ይከታተላል፡፡ በክልሉ ውስጥ በሚመረቱ ዘሮች እና የፀረ ተባይ ኬሚካልና የአፈር ማዳበሪያ ላይ ጥራትን ለማረጋገጥ
በመስክና በክምችት ናሙና ተወስዶ እንዲመረመር ያደርጋል፣ በጥራት ደረጃ መስፈርት መሰረት የጥራት
ደረጃውን ያሟላውንና ያላሟላውን ይለያል፣ የሁሉንም ዘር ደረጃዎች መለያ ምልክት (ታግ) ለይቶ ለተጠቃሚዎች
እስኪደርስ ድረስ ሂደቱን በባለቤትነት ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፡፡ ለፀረ ተባይ ኬሚካል፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ ዘር
አምራቾች፣ አዘጋጆች አቅራቢዎች፣ ሻጮችና ተጠቀሚዎች፤ በጥራት ደረጃዎች አጠባበቅና በአዋጆች በማስፈፀሚያ
ደንቦችና መመሪያዎች አተገባበር ረገድ ስልጠናዎች እንዲሰጡ፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች እንዲነደፉ
ያደርጋል፡፡ የጥራት መጓደልን አስመልክቶ ከተጠቃሚዎች ለሚነሱ ማናቸውም ቅሬታዎች የተጠኑ ምላሾችን
ይሰጣል፡፡ ምርታማነታቸውና ውጤታማነታቸው የወረደ ዘሮች፣ ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችና ማዳበሪያዎች ከስርጭት
እንዲወጡ ያደርጋል፡፡ በመስክና በክምችት የጥራት ቁጥጥር ተካሂዶባቸው የጥራት ደረጃ መስፈርቶችን ያላሟላ
ዘር፣ ፀረ-ተባይ ኬሚካሎችና ማዳበሪያዎች አጠቃቀምና አወጋገድ ይከታተላል፣ የዘርና ሌሎች ግብዓቶችን ጥራት
ቁጥጥርና የማረጋገጥ ጉዳዮችን አስመልክቶ የስራ ክልሉን ይወክላል፤ በስራ ክልሉ ውስጥ የሚካሄድ ህገ ወጥ የዘር፣
ፀረ ተባይና ማዳበሪያ ንግድና ዝውውርን ይከታተላል፤ ህገ-ወጦችን ከሚመለከታቸው የህግ አካላት ጋር በመሆን
ለህግ እንዲቀርቡ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡
በመሆኑም ቅ/ጽ/ቤቱ በአሁኑ ሰዓት የመስክ ሰብል፣ የአትክትና ፍራፍሬ፣ የደንና መኖ ዘር፣ የፀረ ተባይና ማዳበሪያ
ጥራትን በመስክና በላብራቶሪ የመቆጣጠር ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በእፅዋት ዘር ማባዛት፣ ማምረት፣
ማዘጋጀት እና በግብይት፣ ፀረ ተባይና ማዳበሪያንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ የግልም ሆነ የመንግስት ዘር አምራቾችና
አቅራቢዎች ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የመስጠት፣ የማደስ፣ እንዲሁም ህጋዊ አሰራሮችን ያልተከተሉ
ሆነው በሚገኙበት ጊዜ የመሰረዝ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡:

Scroll to Top