የእፅዋት ጤናና ምርት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት/ Plant health and product quality control directorate ዝርዘር ተግባራት

Mr. Moges Zewdu

Plant health and product quality control directorate Director

ዳይሬክቶሬቱ ለእፅዋት ኳራንታይን፤ ለፀረ ተባይና ማዳበሪያ ጥራት ቁጥጥር የሚረዱ የህግ ማአቀፎችን
ከሚኖረው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ወቅታዊ ያደርጋል፣ መተግበራቸውን ይከታተላል፤ ከሚመለከተው ጋር
በመሆን ክልላዊ የእፅዋት ኳራንቲን (Regional Quarantine) ስርዓት በክልሉ እንዲተገበር ያደርጋል፤
አስፈላጊ መግቢያና መውጫ በሮች ላይ የቁጥጥር ጣቢያዎች እንዲከፈቱ ያደርጋል፤ ያደራጃል፣ አፈፃፀሙን
ይከታተላል፤ ከብሄራዊ የእፅዋት ኳራንቲን ሰርዓት ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን መንገድ ያመቻቻል፣
ያስተባብራል፤ መረጃዎችንም ይለዋወጣል:: ዳይሬክቶሬቱ ወደ ክልል ውስጥ የሚገባ ዕፅዋት፣ ዕፅዋት
ውጤቶችና ማንኛውም ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቁሳቁሶች በደንብና መመሪያ የተቀመጡትን መስፈርቶች
አሟልተው መሆኑን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣ የእፅዋት ኳራንቲን ተባይ ይዘው መገኘታቸው በምርመራ
ከተረጋገጠ የማከም፣ የማስወገድ ወይም ወደ መጣበት ክልል የመመለስ እርምጃ እንዲወሰድ ውሳኔ
ይሰጣል፡፡ በመሆኑም እርምጃ አወሳሰዱን በተመለከተ የፋይቶሳኒተሪ እርምጃ ማሳወቂያን በተከተለ
መልኩ ለላኪው ክልል ወይም አካል ይልካል፣ ለአፈጻጸሙ በተላከው ግብረ መልስም መሰረት ክትትል
ያደርጋል፤ ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና መረጃዎች ወቅታዊ ምላሽ ይሰጣል፡፡  ተጨማሪ

Scroll to Top