Plant seed quality control Directorate/የእፅዋት ዘር ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዝርዝር ተግባራት

Mr. Gurmessa Ejeta
Plant seed quality control Directorate Director
ዳይሬክቶሬቱ በክልሉ ውስጥ ሁለንተናዊ የእፅዋት ዘር ስርዓት እንዲተገበርና ጥራት ቁጥጥር ስርዓትን
ለማሻሻል የሚረዱ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ይቀርፃል፤ በእፅዋት ዘር ማምረትና ግብይት ስራ ላይ የተሰማሩ
በሀገሪቱ ህግ መሰረት መስራታቸውን ይከታተላል ያረጋገጣል፤ በስራ ክልሉ ውስጥ ዘርን
በማባዛት፣በማምረት ፣በማዘጋጀት እና በግብይት ንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ የግልም ሆነ የመንግስት ዘር
አምራቾችና አቅራቢዎች ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ያድሳል፣ ህጋዊ አሰራሮችን
ያልተከተሉ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ ይሰርዛል፡፡ በስራ ክልሉ ውስጥ በዘር ማምረት፣ በማባዛት ወይም
በግብይት ስራ ላይ የተሰማራ ማንኛውም ሰው አስተማማኝ የጥራት ቁጥጥር እየተካሄደበት መሆኑን
ያረጋግጣል፡፡ በዘር ማምረት ስራ ላይ ለተሰማሩ አካላትና ለጥራት ቁጥጥር ባለሙያዎች ለጥራት ቁጥጥር
የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስራዎች መካሄዳቸውን ይከታተላል፡፡ በክልሉ ውስጥ በሚመረቱ ዘሮች ላይ
በመስክና በክምችት ናሙና ተወስዶ እንዲመረመር በማድረግ ጥራቱን ያረጋግጣል፣ የሁሉንም ዘር
ደረጃዎች መለያ ምልክት (ታግ) ለይቶ ለተጠቃሚዎች እስኪደርስ ድረስ ሂደቱን በባለቤትነት ያስተዳድራል፣
ይቆጣጠራል፡፡ ለዘር አምራቾች፣አዘጋጆች አቅራቢዎች፣ ሻጮችና ተጠቀሚዎች፤ በጥራት ደረጃዎች
አጠባበቅና በአዋጆች በማስፈፀሚያ ደንቦችና መመሪያዎች አተገባበር ረገድ ስልጠናዎች እንዲሰጡ፤
የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች እንዲነደፉ ያደርጋል፡፡ የጥራት መጓደልን አስመልክቶ ከተጠቃሚዎች
ለሚነሱ ማናቸውም ቅሬታዎች የተጠኑ ምላሾችን ይሰጣል፡፡ ምርታማነታቸውና ውጤታማነታቸው
የወረደ ዘሮች ከስርጭት እንዲወጡ ያደርጋል፡፡፡ ተጨማሪ
