ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የግብርና ግብዓት መጠቀም እስካልቻልን ድረስ የግብርና ልማትን በዘላቂነት ማረጋገጥ አይቻልም”

“ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የግብርና ግብዓት መጠቀም እስካልቻልን ድረስ የግብርና ልማትን በዘላቂነት ማረጋገጥ አይቻልም”

አቶ አጀበ ስንሻው የአብክመ ግብርና ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ

የአብክመ የግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን በ2017 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ከቅ/ፅ/ቤት ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር ግምገማ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዕቅድ አፈፃፀም መድረኩ ላይ የተገኙት የግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የግብርና ግብዓት መጠቀም ወሳኝ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡

የግብርና ግብዓቶችን ጥራት ለማስጠበቅ ባለስልጣን መ/ቤቱና በተዋረድ የሚገኙ ቅ/ፅ/ቤቶች ስለሚሰሯቸው ስራዎችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በግብርና ግብዓቶች ላይ የሚስተዋለውን ህገ-ወጥነት ለመከላከል በቅንጅት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ በቀጣይ ቢሮውና ባለስልጣን መ/ቤቱ በቅንጅትና በትብብር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሯቸው ስለሚገቡ ተግባራት በዝርዝር አንስተዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top