የአብክመ የግብርና ጥራትና ደህነት ባለስልጣን በባ/ዳር ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ በፀረ-ተባይ ኬሚካል ንግድ ላይ ለተሰማሩ ቸርቻሪና ጅምላ አከፋፋዮች የፀረ-ተባይ ኬሚካል አያያዝ፣ምንነት፣የሚያስከትለው ጉዳትና እንዲሁም አዋጅ፣ደንብ እና መመሪያዎች በተመለከተ ግንዛቤ አስጨብጧቸዋል፡፡
በመድረኩ የባለስልጣኑ ም/ሃላፊ የሆኑት አቶ ዘላለም ልየው እንደገለፁት አሁን ባለው ሁኔታ የፀረ-ተባይ ኬሚካል አያያዝና አጠቃቀም በአገር አቀፍ ደረጃም ጭምር ከፍተኛ ውድቀት እያስከተለ በመሆኑ ይሀንንም ችግር ለመቅረፍ በፀረ-ተባይ ኬሚካል ንግድ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች የፀረ-ተባይ ኬሚካል አዋጅ፣ደንብ፣መመሪያ ላይ በቂ ግንዛቤ ይዘው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ም/ሃላፊው አያይዘውም ባለስልጣኑ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ሃላፊነት ለመወጣትና ፀረ-ተባይ ኬሚካል በማህበረሰቡ ዘንድ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል ሲባል ህግና መመሪያን አክብረው በማይሰሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በመድኩ የተገኙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በእውቀት ላይ ተመስርቶ ስራቸውን ለመስራት ያስችላቸው ዘንድ ግንዛቤ መፈጠሩ ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን የፀረ-ተባይ ኬሚካል አያያዝና አጠቃቀም ላይ እያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ እኛ ባለሙያዎች ከምንሰጠው ምክረሃሳብ በላይ ዋናው የኤክስቴሽን ስራ ትልቅ አቅም ስለሚኖረው በስፋት እንዲሰራበት ማድረግ ቢቻል እንዲሁም በቀጣይም እንደዚህ አይነት መድረኮች ሲፈጠሩ ከባለሙያዎች በተጨማሪ ባለሃብቶችም አብረው ተገኝተው ግንዛቤ ማግኘት ቢቻል መልካም ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡





