የግብርና ጥራትና ደህነት ባለስልጣን በ2017 የበጀት አመት ከመስክና ከመኸር ሰብሎች የጥራት ቁጥጥር ከተደረገበት12,720 ሄ/ር የዘር ማሳና 341,470 ኩ/ል በሚገመት የዘር ምርት ላይ የዘር ጥራት መስፈርትን ደረጃ ያሟላ 12,144.3 ሄ/ር የዘር ማሳና 333,799.3 ኩ/ል ምርት መገኘቱን ባለስልጣኑ አስታወቀ፡፡

በባለስልጣን መ/ቤቱ የዘር ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ጉርሜሳ እጀት የዳይሬክቶሬቱን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በመስክ የዘር ጥራት ቁጥጥር ከተደረገበት የዘር ማሳ ውስጥ 98 ከመቶ የሚሆነው ምርት ለዘር አገልግሎት እንዲውል ማድረግ መቻሉን ገልፀው የጥራት መስፈርትን ያላሟላ 575.3 ሄ/ር የዘር ማሳና 7670.3 ኩ/ል ዘር ከዘር አገልግሎት ውጭ እንዲሆን መደረጉን ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በክልሉ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ተጠቅመው ማሳ ድረስ ወርደው የመስክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች መስራት መቻላቸውና ባለሙያው መድረስ ባልቻሉበት ማሳ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት መቻሉ ውጤት ማምጣቱን ገልፀው በቀጣይም ከዘር ውጭ የተደረጉ ዘሮችን ወደ ዘር ስርዓት እንዳይገቡ የቁጥጥር ስርዓቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top