የአብክመ የግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን 2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን እየገመገመ ነው፡፡
በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው የሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላትና የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ ዘላለም ልየው እንዳሉት በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በጥራት ቁጥጥር ስራችን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልፀዋል፡፡ ይህን ችግር ተቋቁሞ አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች በሁሉም ዘርፎች ጥራትን ለማስጠበቅ የተደረገው ጥረት አበረታች እንደነበርም ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም ተቋማዊ አንድነት እና ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ፤ በሁሉም ዘርፎች የሚስተዋለውን ህገ ወጥነት መካላከል ፤ በአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማረም ላይ ትኩረት አድርግን መስራት እንዳለብንም አሳስበዋል፡፡
በዕለቱ የሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የሩብ ዓት ዕቅድ አፈፃፀማቸውን አቅርበዋል፡፡
