የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል የእንቁ ዳጉሳ ማህበረሰብ አቀፍ ዘር ብዜት ስራ
የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል ከሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮጀክት ድጋፍ በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በንጥረ ነገር የበለፀጉ የሰብል ቴክኖሎጅ በማቅረብ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።
በሰቆጣ ወረዳ ለላባ ቀበሌ 48 አርሶ አደር ያቀፈ በ32 ሄክታር መሬት ላይ በ”ጊዜ ወርቅ ምርጥ ዘር አምራች ህብረት ስራ ማህበር” የእንቁ ዳጉሳ ሰብል የብዜት ስራ ተሰርቷል ።
የማህበሩ ሊቀመንበር አርሶ አደር ቄስ ተክላት ገብረ ህይወት በማዕከሉ የቀረበላቸውን የዘር ድጋፍ እና የተግባር ሰልጠና በማግኘታቸው ተጠቃሚ እንደሆኑና የእንቁ ዳጉሳ ሰብል ከሊሎች ሰብሎች በተለየ በረከት በመኖሩ የአመት ቀለባቸውን እንደቻሉ ገልፀው በቀጣይ ከምርምሩ ጎን በመሆን የተለያዩ ቴክኖሎጅ በመጠቀም የበለጠ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ማዕከሉ በዋነኛነት በቆላው አከባቢ የተለያዩ ስራዎች ያሉት ሲሆን በተለይ በሰብል የእንቁ ዳጉሳ በከፍተኛ ደረጃ በአርሶ አደሩ የተወደደ ፤በንጥረ ነገር ይዞታው የተሻለ እና በአከባቢው የተንሰራፍውን የስርአተ ምግብ አጥረትን መቅረፍ የሚችል ሰብል ነው ብለዋል የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አዳነ ባህሩ ፤በማከልም ማዕከሉ ከአሁን ቀደም ያስተዋወቀው” ቆላ አንድ ” የተባለ እንቁ ዳጉሳ መሆኑን አስታውሰው በቀጣይ የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል ከአለም አቀፍ ግብርና ምርምር ተቋም(ICRISAT) ጋር በመሆን ሶስት የእንቁ ዳጉሳ ዘር ለማስለቀቅ ላለፎት ሶስት አመታት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢንስቲትዩቱን መረጃዎች ለማግኘት ከስር ያሉ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ይወዳጁ!
ዌብሳይት፡- www.arari.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100064041610420
ቴሌግራም፦ t.me/ARARIoffical
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@amharaagriculturalresearch147
