በጉዳቱ ልክ ትኩረት ያልተቸረው ኬሚካል
ባህር ዳር የካቲት 27/2017 ዓ.ም (የግ/ጥ/ደ/ባ) የአብክመ የግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን በፀረ ተባይ ኬሚካል አያያዝና አጠቃቀም፣ የህግ ማዕቀፎች፣ አሰራርና አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል። በስልጠናው ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የምትጠቀመው ኬሚካል በመጠን ዝቅተኛ ቢሆንም በብክለት ግን ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ በስልጠናው ተገልፅዋል።
በኢትዮጵያ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱትም አርሶ አደሩ ስለ ፀረ ተባይ ኬሚካል ብክለት ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ ስለመሆኑ ተረጋግጧል።
የተሟላ ግንዛቤ ባለመኖሩ ምክንያትም በሰዎች፣ በእንስሳት፣ በእፅዋት እና በውሃማ አካላት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እየተባባሰ ስለመሆኑ ተገልፅዋል። ባዶ የፀረ ተባይ ኬሚካል መያዣ ዕቃዎችን በአግባቡ ያለማስወገድ እና ለቤት ውስጥ መገልገያነት የመጠቀም ሁኔታም እንዳለም ተነስቷል።
የግብርና ባለሙያዎች ስለ ፀረ ተባይ ኬሚካል አያያዝና አጠቃቀም ለአርሶ አደሩ ተገቢውን የግንዛቤ ፈጠራ ስራ በመስራት በኩል ውስንነት እንዳለም ተገልፅዋል።
በመንግስት በኩል የተሰጠው ትኩረትም የጉዳት መጠኑን የሚመጥን እንዳልሆነ ተገልፅዋል።
በአብክመ የግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን አማካሪ የሆኑት አቶ ጥላሁን አላምነህ ኬሚካል ለምርትና ምርታማነት ጭማሪ አስተዋፅኦ የመኖሩን ያክል በአያያዝና አጠቃቀም ችግር ምክንያት በሰው፣ በእንስሳት እና በአካባቢ ላይ ጉዳት እያስከተለ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ጉዳቱን ለመቀነስ የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እና ሁሉንም የሚዲያ አማራጮች መጠቀም ተገቢ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የአብክመ የግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን ም/ኃላፊ አቶ ዘላለም ልየው በበኩላቸው ለኬሚካል ጉዳቱን የሚመጥን ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ስለመሆኑ ተናግረዋል። አርሶ አደሩ ያለምንም የመከላከያ አልባሳት በሚያደርገው የኬሚካል ርጭት ራሱንና ቤተሰቡን እየጎዳ ነው ብለዋል። ህብረተሰባችንን ከጉዳት ለመታደግ በችግሩ ስፍት ልክ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባልም ብለዋል።





See insights and ads
All reactions:
77
