በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል ሶስት የበቆሎ ዝርያዎችን ከውጭ በማስመጣት አስመዘገበ

በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል ሶስት የበቆሎ ዝርያዎችን ከውጭ በማስመጣት አስመዘገበ

የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል ከ Bio emerging technology institute ጋር በመተባበር ከውጭ ባስገባቸው በIITA

(International Institute of Tropical Agriculture )የበለፀጉ አዲስ የበቆሎ ዘር ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ላለፎት ሶስት አመታት የተሰራ ሲሆን በዚህ አመት በሰርቶማሳያ(Demonstration) በሰቆጣ እና በድሀና ወረዳ በሶስት ቀበሌዎች እየሰራ ይገኛል።

ማዕከሉ ከጎንደር እና ከሲሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል ጋር በጋራ በማስገምገም ሶስቱ የበቆሎ ዝርያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ማስመዝገብ ችሏል።

በሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከል የሰብል ቴክኖሎጅ አቅርቦት ዳይሮክቶሬት አስተባባሪ እና የአግሮኖሚ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ታፈረ ብርሀኑ Betin (PVA) የተባለው የበቆሎ ዝርያ በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ የሰርቶ ማሳያ ስራ የተሰራ ሲሆን ከ 32 እስከ 62 ኩንታል በሄክታር የሚሰጥ አለም አቀፍ ጥራት መስፈርት ያሟላ እና በተለይ በቫይተሚን ኤ (vitamin A) የበለፀገ በመሆኑ

ከሌሎች የበቆሎ ዝርያዎች አንፃር ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው መሆኑን ገልፀዋል

አርሶ አደሮችም በቆሎን በቤታቸው ጓሮ ብቻ በመዝራት ተወስነው እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን በማሳ ደረጃ ከፍ በማድረግ በቆሎን ዋና ሰብል አድርገው ለመዝራት ከፍተኛ ፈላጉት አንዳደረባቸው ገልፀዋል ።

የወለህ 01ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ማሞ ምትኪ ከአሁን በፊት ሲጠቀሙበት ከነበረው ከአከባቢው የበቆሎ ዘር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነት እንዳለው እና በተለይ አከባቢያችን ዝናብ አጠር ስለሆነ የዝናብ ወቅቱም አጭር በመሆኑ በበቆሎ ምርት ለይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳሳደረባቸው ገልፀው

ይህ አዲስ ዝርያ ግን ፈጥኖ ስለሚደርስ ወይም ድርቅን ማምለጥ ስለሚችል ለአከባቢው የአየር ንብረት ተስማሜ መሆኑን ተናግረው የበቆሎው አያያዝ እና ቁመናውም እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

ሌላኛዋ የወለህ 01 ቀበሌ አርሶ አደር ነዋሪ የሆኑት የሽ ወንድማገኝ በሸቱ ወቅት መሸጥ እንደሚያዋጣቸው እና በተለይ ይህ አዲሱ ቀይ በቆሎ ጣፋጭ በመሆኑ ልጆቻቸው ፤ ያአከባቢው ማህበረሰብ በሙሉ እንደወደዱት ተናግረዋል ።

አርሶ አደሮችም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳደረባቸውና በቀጣይ በስፋት እንዲጠቀሙ አዲሱ የበቆሎ ዘር በበቂ እንዲቀርብላቸው የሰቆጣ ዝናብ አጠር ግብርና ምርምር ማዕከልን አሳስበዋል።

የኢንስቲትዩቱን መረጃዎች ለማግኘት ከስር ያሉ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ይወዳጁ!

ዌብሳይት፡- www.arari.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=100064041610420

ቴሌግራም፦ t.me/ARARIoffical

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@amharaagriculturalresearch147

ትዊተር- https://twitter.com/AmharaResearch

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top