Welcome To ANRS Agricultural Quality and Safety Authority
አቶ ፈንታሁን ስጦታው ፈለቀ
የባልስልጣን መ/ቤቱ ኃላፊ
የግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን ኃላፊ መልዕክት
የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ ጥራትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የግብርና ግብዓት መጠቀም ድርሻው የጎላ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ይሁን እንጅ የክልላችን አርሶ አደር እየተጠቀመ ያለው የግብርና ግብዓት በመጠን አነስተኛ ከመሆኑም በላይ አብዛኛው ግብዓት በተጠናከረ የጥራት ቁጥጥር ስርዓት ያለፈ አልነበረም፡፡ ይህም የክልሉ ምርትና ምርታማነት በሚፈለገው ልክና ፍጥነት እንዳያድግ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ የክልሉ መንግስትም ይህን በመረዳት በግብርና ግብዓቶች ላይ የጥራት ቁጥጥር ስርዓትን በባለቤትነት
የሚያስተባብር ተቋም በአዋጅ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቱ የግብርና ጥራትና ደህንነት
ባለስልጣንን በአዋጅ ቁጥር 208/2006 እንዲቋቋም አድርጓል፡፡ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የሰው ሃይሉን በማሟላት ቢሮውን በማደራጀት የፊዚካልና የፋይናንሻል ዕቅዶችን በማቀድ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ ይህ በመደረጉም በግብርና ግብዓቶች ላይ ይስተዋል የነበረው የጥራት መጓደል ችግር በእጅጉ ተሻሽሏል፡፡
በቀጣይም ያሉንን አቅሞችና ልምዶች ተጠቅመን፤ ከሌሎች አጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር ያለንን ቅንጅታዊ
አሰራር ይበልጥ በማጠናከር በግብርና ግብዓቶች ላይ የሚስተዋለውን ህገ ወጥነት እና የጥራት መጓደል
ችግሮች በመቅረፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ የድርሻችንን አስተዋፅኦ
ለማበርከት ዝግጁ መሆናችንን ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡
ጥራቱ የተረጋገጠ የግብርና ግብዓት ለላቀ ምርታማነት
ራዕይ
•በ2027 ጥራቱ የተረጋገጠ የግብርና ግብዓት የሚጠቀም ለጥራት ዋጋ የሚሰጥና ገቢው ያደገ ህብረተሰብ ተፈጥሮ ማየት
]
•Seeing a society that utilizes quality assured agricultural inputs, values quality, and has grown income by 2027 EC
ተልዕኮ
• በክልሉ አስተማማኝ የጥራት ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የግብርና ግብዓቶችን ጥራት በመስክና በላብራቶሪ በመቆጣጠር፣ የእፅዋት ኳራንታይን ተባዮችን በመከላከል ጥራቱ የተረጋገጠ ግብዓት ለተጠቃሚው እንዲደርስ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ
• By establishing a reliable quality control system in the region, through regulating the quality of agricultural inputs in the field and in the laboratory as well as preventing plant quarantine pests to guarantee the user for production and productivity boosting.
ዕሴቶች
• ታማኝነት መለያችን ነው፡፡ • በቅንነት እንሰራለን፡፡ • ግልጽነት መታወቂያችን ነው፡፡ • በቁርጠኝነት ራዕይና ተልዕኳችንን ለመፈፀም እንተጋለን፡፡ • በተጠያቂነት ስራችን እንፈፅማለን፡፡ • በሀቀኝነት እናገለግላለን፡፡ • ስልጣንን በአግባቡ እንጠቀማለን፡፡ • ሁሉንም ያለ አድሎ እናገለግናለን፡፡ • በኃላፊነት እንሰራለን፡፡ • ጥራት መለያችን ነው፡፡ • በህዝባዊ ወገንተኝነት ስሜት እንቀሳቀሳለን፡፡ • ሙስናን፣ ሌብነትን፣ ብልሹ አሰራርንና ስግብግብነትን አጥብቀን እንዋቀጋለን፡፡ • ለሴቶች፣ ወጣቶች እና ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፡፡
Recent News
https://aqsa.gov.et/wp-content/uploads/2025/07/Seed-requlation-375-2016-new.pdf
Read Moreበባለስልጣን መ/ቤቱ የዘር ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ጉርሜሳ እጀት የዳይሬክቶሬቱን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት...
Read More